Post Thumbnail
የዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የቦርድ ስብሰባውን አካሄደ!

መድረኩን የስልጤ ዞን አስተዳዳሪና የዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዘይኔ ቢልካ የመሩት ሲሆን የኮሌጁ ዲን የሆኑት ኢንጂነር አብዱረህማን ሽፋ የኮሌጁን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና ኮሌጁን ይበልጥ ለማደራጀት እንዲሁም ለማሳደግ መነሻ ዕቅድ በዝርዝር አቅርበው ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል።

ኮሌጁ ከጊዜ ወደ ጊዜ እራሱን እያሻሻለና ደረጃውን እያሳደገ መሆኑን በውይይቱ የተገለፀ ሲሆን በዘንድሮው በጀት ዓመት ይበልጥ የኮሌጁን አቅም ለማሻሻልና ለማጠናከር የአካባቢው ማህበረሰብ እና ተወላጆች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ተመላክቷል።

በተጨማሪም በርዱ ለኮሌጁ የገቢ አሰባሰብ ንቅናቄ በመፍጠር እና በህብረተሰብ መዋጮ ለመደገፍ የሚያስችል ውሳኔ አስተላልፏል።

በመድረኩ የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና የኮሌጁ ቦርድ አባል አቶ ሀቢብ ከድር፣ የስልጤ ዞን ቴክኒክና ትምህርት እና ስልጠና መምሪያ ሀላፊና የኮሌጁ ቦርድ ፀሀፊ አቶ ፈድሉ ከድር፣ የወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ ቡላድ ናሙዝ፣የሁለቱም መዋቅር የኢንተርፕራይዝ ሀላፊዎች እና የኮሌጁ ም/ዲኖች ተገኝተዋል።

0 አስተያየቶች

አስተያየትዎን ይጻፉልን