Post Thumbnail
የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን ተግባራትን በማስመልከት..

ስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን ተግባራትን በማስመልከት የተደረገውን የድጋፍና ክትትል ተግባራትን እየገመገመ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የእንኳን ደና መጣቹ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የጦራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሁሴን ሱነሞ በንግግራቸው ጦራ ከተማ አስተዳደር ላይ በተሰሩ ስራዎች የመጡ አበረታች ለውጦች የጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት ተግባራት ውጤት መሆናቸውን ገልፀው የተጀመሩ ውጤታማ ስራዎችን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ከንቲባው አክለውም በዛሬው ዕለት የመስክ ምልከታ የተደረገባቸው የወተት ምርት፣በከተማ ደረጃ የበርበሬና ሌሎች ክላስተር ማዕከላትን በመገንባት በተሰራው ስራ ከወተት ምርት አንፃር ለተለያዩ ግልጋሎቶች የሚውለው ምርት ከከተማው ባሻገር ለሌሎች አካባቢዎችም መትረፍ ወደምንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰና ሲሉ ገልፀዋል።

መድረኩን በማስመልከት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ነዒማ ሙኒር ባስተላለፉት መልዕክት የዚህ የውይይት መድረካችን ዋናው አላማ ባለፉት ጊዜያ እንደ ዞን ለሱፐርቪዥን በተሰማራው ቡድን በየመዋቅሮቹ የታዩ ጉድለቶችን ለማረምና የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በሁሉም መዋቅሮቻችን ለማስፋት ነው ብለዋል።

ኃላፊዋ አያይዘውም በሁሉም መዋቅሮች በየዘርፎቹ የተከናወኑ አበረታች ተግባራትን በማስቀጠል የታዩ ጉድለቶችን ፈጥነን ለማረም በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አንስተው ለዚህ ደግሞ የፓርቲውን አደረጃጀቶች ከምንጊዜውም በላይ ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።

በየመዋቅሮቹ የመጡ ሪፖርቶችን አስመልክቶ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በአቶ ሳሊ ሀሰን በኩል እየቀረበ ይገኛል።

በቀጣይም በቀረበው ሪፖርት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመምከርና ተግባቦች በመፍጠር ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

0 አስተያየቶች

አስተያየትዎን ይጻፉልን