
በወረዳው በቢላሎ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ካሚል መሀመድ የወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን በአርሶ አደሩ ጓሮ ተገኝቶ ምልከታ በአደረገበት ወቅት እንደገለጹት የአፕል ችግኝ በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አትክልትና ፍራፍሬን በሰፊው ለምግብነት እንደሚጠቀሙም የገለጹት አርሶ አደር ካሚል ከምግብነት ባለፈም ለገበያ በማቅረብ በዓመት እስከ 60 ሺህ ብር በላይ እንደሚያገኙ ጠቅሰው የ30፣40፣30 የፍራፍሬ ልማትን በመከተል እስካሁንም 140 የአፕል ዛፎች በመትከል ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡
በዚህም ልጆቻቸውን ያስተምራሉ፤ የተሻለ ኑሮም እየኖሩ መሆኑን ገለጸው በአገኙትም ገቢ አዲስ ቤት እየገነቡ እንደሚገኙ ለወረዳው መንግሥት ኮሙኒኬሽን ተናግረዋል።
ወረዳው ለደጋ ፍራፍሬ ተስማሚ የአየር ንብረት ያለው በመሆኑ በአፕል ልማት የኢኮኖሚ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ እንዳገዛቸው የሚኖገሩት አርሶ አደሮች አቶ ድልሰቦ ኑሪና አቶ በኑር ሳሊያ ናቸው።
እንደ አርሶ አደሮቹ እንደገለጻ የአፕል ምርት ትኩረት እያገኘ በመምጣቱን አፕልን መትከል ቋሚ ተግባር አድርገው እያለሙ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በተለይም 30፣40፣30 የፍራፍራ ልማት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው ልማቱን አሁን ካልበት ወደተሻለ ደረጃ በስፋት ለማልማት የውሃ እጥረት እንቅፋት እንደፈጠረባቸው አውስተው የሚመለከተው ባለድርሻ አካል ለችግሩ መፍትሄ እንዲያበጅለት ተናግረዋል።
እንደ ወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት መረጃ 65 በመቶ የሚሆነው አርሶ አደር በጓሮው አፕልን ያለማል። ከዚህ በፊት ከሌላ አካባቢ ይመጣ የነበረውን የአፕል ችግኝ በከፊል በወረዳው በማልማት ለአርሶ አደሮች እየተሰራጨም እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ ።
በወረዳው 625 ሄክታር መሬት በአፕል ዛፎች የተሸፈ ሲሆን በአማካይ በዓመት 13 ሺህ 7መቶ 50 ኩንታል ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አስተያየትዎን ይጻፉልን