
የቱሪዝም መዳረሻዋ ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መገኛ ስፍራ ናት።
ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በስልጤ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዷ ስትሆን ወረዳዋ በጥንታዊ መስጂዶች፣ በሰው ሰራሽ ዋሻዎች፣ በፏፏቴዎች እና በተለያዩ ደኖች የታደለች ባለጸጋ ምድር ነች።
በዛሬው ዘገባችን የወረዳው ርዕሰ መዲና ከሆነችው ቂልጦ ከተማ በስተደቡብ ምዕራብ በቅርብ ርቀት የሚገኘውን ማራኪ ደን ነው።
ይህ ደን በውስጡ ጎርተና ዋሻ፣ ፏፏቴ ይገኙበታል፣ ደኑን የተለያዩ የዱር እንስሳት የሚገኙበት ሲሆን አዋፋቶች በዝማሬያቸው በእጅጉን አስውበውታል።
አስተያየትዎን ይጻፉልን