የስልጤ ብሔረሰብ አፍ መፍቻ ቋንቋ

የስልጤ ብሔረሰብ አፍ መፍቻ ቋንቋ ስልጢኛ ሲሆን ከሴማዊ የቋንቋ ቤተሰብ ይመደባል፡፡ ቋንቋው ከአረብኛ፣ ከጉራጊኛ ፣ ከሐረሪ፣ ቋንቋዎች ጋር ይመሳሰላል፡፡ የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ በከተሞች አካባቢ ያሉ አማርኛን እንዲሁም እንደ አጐራባችነታቸውና ቅርበታቸው የሀድይኛ፣ የማረቆኛ፣ የጉራግኛ፣ የኦሮምኛ እና የሀላብኛን ቋንቋዎች በሁለተኛ ደረጃ ይናገራሉ፡፡ ሌሎችም አጐራባች ብሔረሰቦች እንዲሁ የስልጢኛን ቋንቋ እንደየቅርበታቸው ለመግባቢያነት ይጠቀማሉ፡፡

ስልጢኛ ከ60 ዓመት በፊት የአረብኛ ፊደልን በመጠቀም ለጽሑፍ የዋለ ቋንቋ ቢሆንም ከ1967 ዓ/ም ጀምሮ ልዩ ልዩ አዋጆች እና የመሰረተ ትምህርት ማስተማሪያ መጽሐፍት የሳባ ፊደልን በመጠቀም በቋንቋው ተተርጉመዋል፡፡ ከ1987 ዓ/ም ጀምሮ የ1ኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሣይክል የመማሪያ መጽሐፍት በቋንቋው ተዘጋጅተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የትምህርት ቋንቋ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ እንደዚሁም የሣባ ፊደልን በመጠቀም የመማሪያ መጽሐፍት፣ የስልጢኛ መዝገበ ቃላት፣ የስልጤ ሕዝብ ታሪክ እና ሌሎች መጽሀፍቶች በቋንቋው ተጽፈው አገልግሎት እየሠጡ መሆናቸው ቋንቋው በማደግ ላይ ያለ ስለሚሆኑ የሚገልፁ እውነታዎች ናቸው፡፡

ስልጥኛ ቋንቋን የበለጠ ለማወቅና ለመማር ከፈለጉ Siltigna Dictionary መተግበሪያ ከፕሌይ ስቶር ያውርዱ!