የስልጤ ዞን መስተዳደራዊ መዋቅር

የስልጤ ዞን አጠቃላይ 2700.04 ስኩዌር ኪ.ሜ ስፋት ያለው ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለእርሻ ያዋለው 198587.05 (165027.27 በዓመታዊ ሰብልና 33557.5 በቋሚ ሰብል የተሸፈነ)፤ ሊለማ የሚችለው 8319፤ ሊለማ የማይችለው 4759.17፤ ለግጦሽ አግልግሎት የዋለ 10646.67፤ ደንና ቁጥቋጦ 29187.47 ውሃና ረግረጋማ ሥፍራ 8832.84 እና የቀረው 12423.72፤ በሌሎች ልዩ ልዩ ይዞታዎች የተሸፈነ ነው፡፡

አስተዳደራዊ አወቃቀርም በ10 ወረዳዎችና በ5 ከተማ አስተዳደሮች ሲሆን (ዳሎቻ፤ ሁልባራግ፤ ስልጢ፤ ምስራቅ ስልጢ፤ ላንፉሮ፤ ሚቶ፤ አሊቾ-ውሪሮ፤ ሳንኩራ፤ ምዕራብ አዘርነት በርበሬ፤ ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳዎችና ወራቤ፤ ቅበት፤ ጦራ፤ ዓለምገበያ እና ዳሎቻ ከተማ አስተዳደር) የሚገኙ ሲሆን እንዲሁም ዞኑ በ36 የከተማ ቀበሌያትና በ200 የገጠር ቀበሌያት የተደራጀ ነው፡፡

Subscribe ያድርጉ

በየ እለት የሚለቀቁ ዜናዎች ይደርስዎታል