ሀገራችን በየአመቱ በሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር የዉጭ ምንዛሬ አውጥታ የእንጨት ዉጤቶችን ከዉጭ ሀገራት ወደ ሀገራችን እንደምታስገባ ይታወቃል። በዞናችን ሰፊ የደንና የተፈጥሮ ሀብት እያለን የገበያ ክፍተቱን አጥንቶ ወደ ዘርፉ የገባ ባላሀብት ዬለም።
በዞናችን ሰፊ ሄ/ር መሬት በደንና በቀርካሃ ተክል የተሸፈነ ሲሆን በደን ሀብታችን ላይ ተመስርቶ ሊቋቋም ከሚችሉ ፋብሪካዎች መካከል ቺፕውድ ፋብሪካና የወረቀት ፋብሪካ ይገኝበታል ከሚያመርቱት ምርቶች መካከል ወረቀትና የወረቀት ዉጤቶች፤ ለፈርኒቸር ምርቶች፤ ቺፕዉድ፣ ፕላይ ውድ፣ ቪነር፣ ሀርድ ቦርድና ማይካ የእንጨት ውጤቶች ምርታቸው ሁሉ በፋብሪካ የሚመረቱ በመሆናቸው ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ ሆነው በጥሬ ዕቃነት ለእንጨት ስራ አምራቾች የሚያቀርቡት ምርቶች ናቸው እነዚህ ኢንዱስትሪዎች አብዛኛዎቹ በአነስተኛ ደረጃ ያሉ ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ በመካከለኛና በከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡
ከቀርካሃ ምርት ዉጤቶች ጋር በተያያዘ የቀርካሃ ተክል ከላይ ለተጠቀሱት የኢንደስትሪ ምርቶች በተጨምሪ ከቀርካሃ በርካታ ምርቶችን ማምረት የሚያስችል ሰፊ እድል አለ፡፡ በተለየ መልኩ ከቀርካሃ ከሚመረቱት ምርቶች ስንመለከት የተለያዩ የቤት ውስጥ መገልገያዎች ወረቀትና የወረቀት ምርቶች፡ የተለያዩ፡ጌጣጌጦች፤ የሱፍራ መመገብያ ምንጣፎች ፤ እስቲኪኒ፤ ሰንደል ወዘተ በአንድ ኢንደስተሪ በቀርካሃ የሚመረቱ የኢንደስትሪ ምርቶች ናቸው፡፡
የምግብ ዘይት እያንዳንዱ የሰው ልጅ የሚጠቀመው ምርት ሲሆን ሰፊ እና አስተማማኝ ገበያ ያለው ትርፋማ ኢንደስተሪ ነው።
በየ እለቱ ለፍጆታ አገልግሎት ከሚውሉ ሸቀጦች መካከል አንዱ የምግብ ዘይት ነው፡፡ የምግብ ዘይት ከተለያዩ የቅባት እህሎች ፤ የጓሮ አትክልቶች፤ ፍራፍሬዎች የጥጥ ፍሬ፤ አኩሪ አተርና የመሣሰሉ የግብርና ምርቶችን በጥሬ እቃነት በመጠቀም የሚዘጋጅ የኢንዱስትሪ ምርት ነው፡፡ ሀገራችን ለምግብ ዘይት ዝግጅት የሚያገለግሉ የግብርና ጥሬ እቃዎችን በተለይም የቅባት እህሎችን በሰፊው የምታመርት ቢሆንም ዛሬም ደረጃውን ያልጠበቀና ህብረተሰቡን ለተለያየ የጤና እክል የሚያጋልጥ እንደሆነ በጤና ባለሙያዎች የሚነገርበት ከፍተኛ መጠን ያለው የምግብ ዘይት ወደ ሀገራችን ይገባል፡፡ በመሆኑም ባላሀብቶች ወደዚህ ዘርፍ ቢገቡ ተጠቅመው ሊጠቅሙ የሚችሉበት የኢንቨስትመንት አማራጭ ነው።
በሀገራችን ከፍተኛ የበርበሬ ምርት ከሚመረትባቸው አካባቢዎች መካከል ስልጤ ዞን አንዱና ዋነኛው አካባቢ ነው። በሀገራችን በከተሞች አካባቢ የሚኖረው የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የሚገኝ ከመሆኑ በተያያዘ የባልትና ዉጤቶች ማቀነባበሪያ ኢንደስተሪዎች ትርፋማ ከመሆናቸውም በተጨማሪ በገበያ ላይ ያላቸው ተፈላጊነት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ይገኛል።
ዞናችን በርበሬና ሌሎች የባልና ማቀነባበሪያ ጥራጥሬዎችን ከሚያመርቱ አካባቢዎች በቀዳሚነት የሚመደብ ነው፡፡ ለአብነትም ቀይ በርበሬ፣ አተር፣ ባቄላ፣ ገብስ፣ ሽንብራ፣ ቡላና ሌሎች በርካታ የቅመማቅመም ጥሬ እቃዎች በዞናችን በስፋት ይመርታሉ፡፡ የአካባቢያችን በርበሬ ዝርያ ተመራጭ ከመሆኑም በተጨማሪ በአጎራባች ዞኖችም በርበሬና ሌሎች ግብዓቶች በስፋት የሚመርቱ መሆኑ በመስኩ ለሚሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ዞናችን ምቹ መዳረሻ ነው፡፡
ቅመማቅመም ማቀነባበርና የማሸግ ሥራ በጣም ትርፋማ ከሚባሉ የአግሮ ኘሮሰሲንግ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አንዱ ነው፡፡
ባለንበት የግሎባላይዜሽን አለም ላይ ሆነን ወደ ኋላ የኢኮኖሚ ታሪክን ስንመለከት የጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ላደጉ አገራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን በስፋት ያስረዳናል ይህም የሆነበት ምክንያት ዘርፉ ሰፊ የሰው ሀይልን የሚያሳትፍ በመሆኑም በማደግ ላይ የሚገኙ አገራት ወደ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ሲገቡ በጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ቢጀምሩ አዋጭነት እንዳለው ይመከራል፡፡
ወደዚህ ዘርፍ የሚገቡ ኢንቨስተሮች ጥሬ እቃዉን፣ጨርቆችን/የጥጥ ምርቶችን/ክሮችን ወዘተ ከተለያዩ ኢንደስትሪዎች በቀላሉ እና በብዛት ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የገበያም ሁኔታው አስተማማኝ እና እያደገ የሚሄድ ትርፋማ የኢንቨስትመንት አማራጭ ነው።
የፕላስቲክ ምርቶች በአብዛኛው የሚጠቀሙት ግብዓት የፋብሪካ ምርቶች ሲሆን በተጨማሪነት ያገለገሉ የፕላስቲክ ምርቶችንም ይጠቀማል፡፡አመራረቱም የተለያዩ ሞልዲንግ ማሽን በመጠቀም በቀላል ሂደት የሚመረት ነው፡፡ ከፕላስቲክ የሚሰሩ ወንበር፣ጠረጴዛ ፣ቅርጫትና የመሳሰሉት ምርቶች ደን እንዳይጨፈጨፍ በማድረግ የአካባቢ ጥበቃንም የሚያበረታታ ይሆናል፡፡
አብዛኛው ማህበረሰብ የሚገለገልባቸው ምርቶች መሆኑ የገበያ ፍላጎት ክፍተት እንደማይኖር ይታመናል፡፡
ከፍተኛ እውቀትና ቴክኖሎጂ በመጠቀም በጥንቃቄ የሚመረት የኢንደስተሪ አማራጭ ነው። ዘርፉ የሚጠቀመው አብዛኛው ግብዓት ከሌሎች ኢንደስተሪዎች የሚገኝና የግብርና ዉጤቶችን ሲሆን ምንም የገበያ ችግር የሌለበትና ትርፋማ ዘርፍ ነው።
የዞናችን ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ለሞጆ ደረቅ ወደብ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ የብረታብረት ኢንዱስሪ ግብዓቶችን በቀላሉ ለማግኘትና ለማስገባት የሚያስችል መሆኑ በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡
የተመረቱ ምርቶችንም ወደተለያዩ ገበያዎች ለማቅረብ ስልጤ ዞን መዕከላዊ ዞን እንደመሆኑ ወደዘርፉ የሚገቡ ኢንቨስተሮች የገበያ ስጋት እንደማይገጥማቸው ይታመናል፡፡
የኮስሞቲክስ ሜካፕ ኢንደስትሪ በአመት በቢሊዮኖች ዶላር የሚንቀሳቀስበት ትርፋማ የማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ ነው፡፡ ዘርፉ በየግዜው እየተሻሻለና እየዘመነ አዳዲስ ፎርሙላዎችና አሰራሮች የሚታዩበት የተሸሻሉ ምርቶች የሚመረቱበት መስክ ነው፡፡ በኮስሞቲክስ ኢንደስትሪ አለም ግብአት ሲባል በ3 ይከፈላል እነሱም functional /መስርያ ለስራ የተዘጋጀ ዋናው ግብአት/ ,Aesthetic /ለምርቱ ስነ ውበት መጨመርያ/ and claims /የባለቤትነት ማስጠበቅያ/ በሚል የሚከፈሉ ሲሆን፡፡ አሁን በዚህ ሰነድ ላይ 7 አይነት ዋና የግብአት አይነቶችን እንመለከታለን
የኮስሞቲክስ ምርቶችን ለማምረት በአብዛኛው ከኬሚካል ግባአቶች ማምረቻ ኢንደስትሪዎች የሚመረቱ የኬሚካል ምርቶችን የምንጠቀም ነው የሚሆነው፡፡
በሀገራቸን ከ80% በላይ አርሶአደር የሚኖርባት እንደመሆኗ እና አብዛኛው አ/አደር ከፊል አርብቶ አደርም እንደመሆኑ መጠን የእንስሳት መኖ ፍላጎት በሂደት ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም በእንሰስሳት እርባታ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚሰማሩ ባለሀብቶች በዞናችን እየጨመረ መምጣቱ የዘርፉን የገበያ ፍላጎት ከፍ ያደርገዋል፡፡ ስለሆነም የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ አዋጭ የኢንቨስትመንት መስክ ነው፡፡
የቸኮሌትና ከረሜላ ማምረቻ ፋብሪካ ብዙ ካፒታል የማይፈልግ በተመጠጣኝ ካፒታል ሊመሰረት የሚችል ኢንደስትሪ ሲሆን በገበያም ውስጥ ዘውትር የሚፈለግ ትርፋማ ኢንደስትሪ ነው፡፡
የደረቅ እና ፈሳሽ ሳሙና ግብአቶች በሀገር ውስጥ ገበያም ከሀገር ውጪ ከሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚገባ ሲሆን ግብአቱ እንደ ሀገራችን በተቋቋሙ የኬሚካል ኢንዱስትሪዎች እና ኬሚካሎችን ከሀገር ውጪ በሚያስመጡ ጅምላ ነጋዴዎች የሚቀርብ ነው፡፡ የኬሚካል ምርቶች ህብረሰቡ በየእለቱ የሚገለገልባቸው እንደመሆናቸው ከፍተኛ የገበየ ፍላጎት ያላቸው ምርቶች ናቸው፡፡
ዞናችን ስንዴ አምራች ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ መሆኑና ከኦሮሚያ ክልል ዞኖችና ሌሎች አጎራባች ዞኖች (አርሲ፣ባሌ፣ሀዲያ፣ከምባታና፣ሌሎችም) ኣካባቢዎች የሚመርተውን የስንዴ ምርት በቀላሉ በግብዓትነት ለመጠቀም የሚያስችል ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ያለው መሆኑ በምግብ ማቀነባበሪያ ዘርፍ ላይ ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሀብቶች ዞናችን ምቹ መዳረሻ ነው፡፡
ከገበያ አንጻርም ምንም እንኳ ባላሀብቶች በሰፊው የተሰማሩበት ዘርፍ ቢሆንም ህብረተሰቡ በስፋት የሚጠቀመው መሰረታዊ ፍጆታ በመሆኑ ገበያው ከህዝቡ ጋር እያደገ የሚሄድና አስተማማኝ ነው ተብሎ የሚወሰድ ነው፡፡
በዞናችን በሁሉም ወረዳዎች ቲማቲም ለማምረት የሚያስችል አግሮ ኢኮሎጂ ያለ ሲሆን በተጨባጭ በዋናነት በስልጢ፤በምስራቅ ስልጢ፣ሚቶ፣ በላንፉሮ፤ በዳሎቻ፤ በሁልባራግና ሳንኩራ ወረዳዎች በሙሉ አቅም ባይሆንም እያመረተ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በአጎራባች ዞኖች እና አጎራባች ኦሮሚያ ክልል እንደ ሀገር ከፍተኛ ቲማቲም የሚመረትበት አካባቢ እንደመሆኑ መጠን ዞናችን በዘርፉ በስፋት እየመረተ የሚገኝ መሆኑ ዞናችን በዘርፉ ለሚሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ምቹና አዋጭ መዳረሻ ነው::
በዞናች እና በአካባቢው ውስጥ ድንች በሰፊው የሚመርት ቢሆንም እስከ ዛሬ ባለው ልምድ ለቤት ውስጥ ፍጆታና በአነስተኛ ደረጃ ለገበያ የሚቀርብ ምርት ነው፡፡ ምክንያቱም የድንች ምርት በጥሬ ደረጃ በባህሪው ከተወሰኑ ወራት በላይ መቆየት የማይችል የስራስር አይነት ነው፡፡ ድንች በዞናችን በተለያዩ ወረዳዎች የሚመረት ሲሆን በተጨማሪም በዞናችን አቅራቢያ በሚገኙት አዋሳኝ አካባቢዎችም በስፋት የሚመረት ሰብል ነው፡፡
ስለሆነም የድንች ምርተትን ወደ ኩኪስ፣ቺፕስ፣ሰላይስ፣ብስኩት፣ ፊኖ ዱቄት፣የድንች ዱቄት፣የልጆች ምግብ ወዘተ የሚያቀነባብር ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ዞናችን ተመራጭ ነው፡፡
በዞናችን በአመት ከሚመረተው ምርት ውስጥ 350 ቶን የማር ምርት ወደ ገብያ ይገባል፡፡ የማር ምርት በዞናችን በተለያዩ ወረዳዎች የሚመረት ሲሆን በተጨማሪም ከዞናችን አዋሳኝ አካባዎችም በብዛት የሚመረት ምርት አለ፡፡ ስለሆነም የማርና ሰም ምርት ማቀነባበርያ ፋብሪካ አዋጭ ዘርፍ ነው፡፡
በተጨማሪም የሻማ ማምረቻ ስራ በመካከለኛ ደረጃ በእጅ አውቶማቲክ በሆኑ ማሽነሪዎች የሚሰራ በመሆኑ በዞናችን ከማር ማቀነባበሪያው እና ከስጋ ምርት ማቀነባበሪያዎች ተሳስሮ መቋቋም የሚችል የማምረቻ ኢንዱስትሪ ተቋም ነው፡፡
የወንዶች የሴቶችና ህጻናት ሽፍን ጫማ የወንዶች የሴቶችና ህጻናት ክፍት ጫማ፣ የተለያዩ አልባሳት(ሱሪ ኮት ጃኬት)፣ቦርሳ ዋሌትና ቀበቶ ምርት በዋናነት በዘርፉ የሚመርቱ ናቸው፡፡ ግባዓቱን ከኢትዮጵያ የኢንደስተሪ ግባዓቶች አቅራቢ ድርጅት ማግኘት ይቻላል።
በአካባቢው በርካታ የዱቄት ፋብሪካዎች ስለሚገኙ እና የተለያዩ ፋብሪካዎች እየተቋቋሙ የሚገኙ በመሆናቸው የማሸጊያ መዳበሪያ ከረጢት ፍላጎት ከፍተኛ ስለሚሆን በዚህ ዘርፍ ላይ ባላሀብቶች ቢሰማሩ የአካባቢውን ገበያ በቀላሉ መቆጣጠር ይችላሉ።
በተጨማሪም በጣም በርካታ ምርቶችን በአንድ ግዜ አጓጉዞ ወደተለያዩ ገበያዎች በማድረስ መሸጥ የሚያስችል ኢንደስትሪ ነው። የማምረቻ ግባዓቱንም ከሀገር ዉስጥ አስመጪዎች አሊያም ከዉጭ ሀገር በማስመጣት ከሞጆ ደረቅ ወድብ በቀላሉ ወደ ወራቤ ማቅረብ የቻላል።
የሲሚንቶ ፋብሪካ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀመው የኮሚቼ መዕድንና የሬዳሽ መዕድን በዞናችን እንደልብ የሚገኝ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በተጨማሪነት የሚያስፈልጉ መዕድናትን ከምዕራብ እና ከመካከለኛው የሀገራችን ክፍል በቅርብ ትራንስፖርት በማቅረብ በዞናችን ሊመረት የሚችል የመዕድን ዘርፍ ላይ የሚካከት ትልቅ የማንፈክቸሪንግ ኢንቨስትመንት አማራጭ ነው።
ግንባታዎችን በቁርጥ ዋጋ ማካሄድ ዘርፎች በሰፊው ሊሰራባቸው ከሚችሉት የኢንቨስትመንት አማራጮች መካከል ዋና ዋናዎቹናቸው፡፡
የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በቅድመ-መደበኛ(ከነርሰሪ እስከ ዩኬጂ)፣የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከ1-8)፣ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከ9-12) እንደ ቅደም ተከተላቸው ሊሰራባቸው ከሚችሉት የኢንቨስትመንት አማራጮች ሲሆኑ በዋናነትም በቅድመ-መደበኛ (ከነርሰሪ እስከ ዩኬጂ) የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ ቢሰራ ማህበረሰቡም በዘርፉ የሚሰማሩ አካላት ውጤታማ እንደሚሆን የተደረገው ፖቴንሻል ጥናት አመላክቶዋል፡፡
በጤናው ዘርፍ በኢንቨስትመንት ጥናት የተመረጡ የፖቴንሽያል አማራጮች አስራ አንድ ሲሆኑ እነሱም የመድሃኒትና የህክምና መገ/መሳ/ ማከፋፈያ ድርጅት ፣ የሃይጅንና ሳኒቴሽን ግብይት አቅርቦት /sanitation marketing/፡-፣ የህዝብ መጸዳጃ ቤትና ሻወር ቤቶች አቅርቦት ፣ የግል ስፔሻሊቲ ክሊኒክ በተለይም የአይንና የጥርስ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ ፣ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፣ የመድሃኒት ፋብሪካ በተለይም የኦክስጅን እና የግሉኮስ ማምረቻ ፣ መድሃኒት መደብር/Druge store/፣ መድሃኒት ቤት /Pharmacy /፣ በወራቤ ሆስፒታል የደም ባንክ ማቋቋም፣ የማህበረሰብ ጤናመድህን በተመረጡ የግል ጤና ተቋማት መጀመር እና IMAGING ማእከል ማቋቋም የሚሉት ዋና ዋናዎች ናቸው::
እንደ ዞናችን ተጨባጭ ሁኔታ በዚህ ዘርፍ ያለው እምቅ አቅም ገና ያልተነካና ያለተዋዳዳሪ ሊሰራባቸው የሚችሉ በርካታ አዋጭና ተመራጭ የኢንቨስትመንት አማራጭ መስኮችን ይዞ የሚገኝ ነው፡፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኘው ዞናችን የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ገበያ በቀላሉ ለማማለልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ በርካታ አንፃራዊ ጥቅሞች ያሉት ዞን ነው፡፡ ስለሆነም በዞናችን በተለይም በቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት /ሎጅ፣ሪዞልት፣ፔንስዮን፣ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል፣ ካፌና ሬስቶራንት፣ የሰርግና የኮንፈረንስ አዳራሾች፣ የመዝናኛ መናፈሻዎችና ሌሎችም በወነኛነት የሚጠበቁ ናቸው፡፡
ዞኑ ካለው የስነ-ምህዳርና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎችን መነሻ በማድረግ ንጽጽራዊ ብልጫ ያላቸውንና የባለሀብቱን ካፒታል ኢንቨስትመንት የሚፈልጉና ኢንቨስት ቢደረግባቸው ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ሊያስገኙ የሚችሉትን የሰብል ዓይነቶችን ከዚህ በታች ለግብርናው ኢንቨስትመንት አማራጭ የኢንቨስትመንት አቅም/ፖቴንሻል/ እንደሚሆኑ ተለይተዋል። እነዚህም፡-
በጥቅሉ የዞኑ ንጽጽራዊ ብልጫ አቅም/ፖቴንሻል/ መሆናቸውን ጥናቱ ለይቷል። በዝርዝር ማሳያቸውም ሲተነተን እንደሚከተለው ተቀምጧል።
በዞናችን በዓመታዊ ሰብሎች ላይ ያተኮሩ የግብርና ልማት ስርዓት የፍራፍሬ ሰብሎችንም ጨምሮ በአርሶ አደሮችና አምራቾች የዓመራረት ስርዓት ዉስጥ ተካቶ እንዲመረትና ህብረተሰቡም ተጨማሪ የስራ እድል በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ የገበያ ተጠቃሚ፣ የተመጣጠነና ተጨማሪ የምግብ አቅርቦት እንዲያገኝ ማድረግ ሲሆን ከፍራፍሬዎችም ዋና ዋናዎቹ በዞናችን በዋናነት እየተመረቱ የሚገኙ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ አፕል፣ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ ፕሪም ወዘተ… ናቸው፡፡
ዞኑ የተለያዩ ስነ-ምህዳር ውስጥ መገኘቱ ለተለያዩ የእንስሳት ሀብት ልማ ምቹ ያደረግዋል፡፡ ዞኑ ውስጥ የመኖ ልማት እና የውሃ አቅርቦት እየተሸሻለ መምጣት የኢንቨስትመንት አቅሙን የበለጠ ያሳድገዋል፡፡ ከነዚህ የስነ-ምህዳርና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎች መነሻ በማድረግ ንጽጽሪ ብልጫ ያላቸውን የእንስሳት አማራጭ ኢንቨስትመንት አቅችን ከዚህ በታችተዘርዝረዋል፡፡
የተለዩ ዋና ዋና የዞኑ የኢንቨስትመንት አቅሞች ናቸው፡፡
በዚህ ዘርፍ ዞናችን ከፍተኛ የተፈጥሮ ሀብት እንደሚኖር የሚገመት ሲሆን በሁሉም መስኮች ተጨማሪና ተከታታይ ጥናቶችን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይሁንና እስከ ዛሬ ባለው እውነታ የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶችና የሚታሸግ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙ የማዕድን ሀብቶቻችን ናቸው፡፡
ከግንባታ ግብዓቶች መካከል አሻዋ፣ ድንጋይ፣ጠጠርና ቦረቦር በዋናነት በዞናችን የሚገኙ ማዕድናት ናቸው፡፡ በሀገራችን የግንባታው ኢንዱስትሪ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያለበት ዘርፍ እንደመሆኑ የነዚህ ማዕድናት የገበያ ፍላጎት እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም ባለሀብቶች ወደ ዞናችን ገብተው ከላይ የተዘረዘሩ ማዕድናትን በማምረት ኢንዱስትሪው መስክ ቢሰማሩ ትርፋማ የሚያደርግ እምቅ አቅም መኖሩ በተደረገው የኢንቨስትመንት አቅም ጥናት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ሌላው በማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ በዞናችን በአዋጭነት የተለየው የንፁህ መጠጥ ዉሃ ማሸግ ኢንዱስትሪ መስክ ሲሆን አዳዲስ ባለሀብቶች ገብተው ቢያለሙ የአቅም ስጋት የሌለበት መስክ እንደሆነ ተጠንቷል፡፡