Post Thumbnail
የክረምቱ ወቅት ሲጠናቀቅ ለፀደይ ቦታውን ይለቃል በዚህም ወቅት የመስኖ አማራጭ..

የክረምቱ ወቅት ሲጠናቀቅ ለፀደይ ቦታውን ይለቃል በዚህም ወቅት የመስኖ አማራጭ በሌለባቸው አካባቢዎች አርሶአደሮች የመደበኛ አዝመራቸውን ሰብስበው ከጨረሱ በኋላ እስከ ቀጣዩ የበልግ እርሻ ወቅት ድርስ ከእርሻ ስራ ውጪ በመሆን ለብዙ ሀብቶች ብክነት ይጋለጣሉ።

የፀደይ ወቅትን መጠቀም ከተቻለ በመደበኛው የእርሻ ጊዜ የለሙ ሰብሎች ተሰብስበው አነስተኛ የውሃ ፍላጎት ባላቸው ሰብሎች ዳግም በመዝራት ተጨማሪ ምርት ለማምረት የሚያስችል የአዝመራ ወቅት ነው፡፡

#በስልጤ ዞን በዘንድሮው ምርት ዘመን አርሶ አደሩን ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር ለፀደይ ሰብል ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት ስነ-ምህዳሩ ምቹ በሆነባቸው መዋቅሮች በተገቢው ለማምረት የሚያስችል ንቅናቄ በየደረጃው እስከ አምራች አርሶአደሮች ድረስ በመፍጠር ወደ ተግባር ተገብቷል።

ከዚህ ቀደም የማምረት ልምድ ባልነበረባቸው አካባቢዎች ጭምር ሰፋፊ ኩታ-ገጠም በሆነ መልኩ የማልማት ስራ የተሰራ ሲሆን በአጠቃላይ በፀደይ ወቅት ከሚለሙ ሰብሎች ሽምብራና ጓያ ጨምሮ በአጠቃላይ 5,041 ሄር በማልማት ከ92ሺ ኩል በላይ ምርት ለማምረት ታቅዶ 6,584 ሄር የለማ ሲሆን ከለማውም ማሳ ከ115ሺ ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።

በሂደቱ ከ20ሺ በላይ አርሶአደሮችን በማሳተፍ በበጋው ወቅት ይባክን የነበረ የሰው ጉልበት ፣ጊዜና ገንዘብ በስራ ላይ ማዋል ተችሏል ። ይህም የለማው የፀደይ ሰብል ልማት አሁን ላይ ተስፈ ሰጪና በጥሩ ቁማና ላይ ይገኛል፡፡ በአርሶ አደሮች ከፍተኛ መነቃቃት የፈጠረ ነው ተብሏል፡፡

0 አስተያየቶች

አስተያየትዎን ይጻፉልን