Post Thumbnail
‎በስልጤ ዞን ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እና ዞን አቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው.

‎በፎረሙ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ብልካን ጨምሮ ሌሎች የዞን፣የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ባለሀብቶች ተሳትፈውበታል።


በዚህ ዞናዊ ልዩ የኢንቨስትመንት ፎረም ‎በዞኑ አጠቃላይ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች፥ የዞኑ እምቅ የኢንቨስትመንት አቅሞች እና በዘርፉ ማነቆዎችና የትኩረት መስኮች ላይ ከባለሀብቱና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር የሚመከርበት እንደሆነ ተነግሯል።


‎በዝግጅቱ ላይ እስካሁን ያሉ የኢንቨስትመንት ስራዎችና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ምክክር እየተደረገበት ይገኛል።

Wath a video
image

0 አስተያየቶች

አስተያየትዎን ይጻፉልን