አባያ/ጡፋ ሐይቅ የሚገኘው በስልጢና በላንፉሮ ወረዳዎች መካከል ሲሆን የውሃ ዋና የሚችልና ነፋሻማ አየርና ሰፊ የውሃ አካል ማየት የሚፈልግ መኪናውን አዘጋጅቶ ከወራቤ በስተ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 42 ኪ/ሜ ተጉዞ መድረስ ይችላል፡፡ የስልጢ ወረዳ ዋና ከተማ ቅበት ከደረሱ በኃላ 15 ኪ/ሜ በምስራቅ አቅጣጫ ይርቃል ለጀልባ መዝናኛ ምቹ የአሳ ምርትም ያለዉ ነው፡፡ ሐይቁን የበለጠ ማራኪ የሚደረገው ደግሞ የስምጥ ሸለቆ መለያ የሆነ አዕዋፋት በብዛት የሚገኙበትም በመሆኑ ነው፡፡ ባለሀብት ከሆኑም ቦታዉን ሲጎበኙ በኢኮ -ቱሪዝም (በሎጅ ኢንቨስትመንት) ለመሰማራት ምኞትና ዕቅዱ ይኖሮታል፡፡