የስልጤ ዞን የባህል ሙዚየም

የስልጤ ዞን የባህል ሙዚየም የቤቱ ግንባታ ዙሪያው ባለ 5 ጎጆ ቅርፅ ያለው፤በአንድ ትልቅ ምሶሶ እና ለ5ቱ ጎጆዎች በአምስት አነስተኛ ምሶሶ የተሰራ ሲሆን የዚህ ግንባታ አሰራር 5ቱ የጎጆ ቅርፅ ስያሜው በአምስቱ የስልጤ ቀደምት እናቶች በሆኑት ጊስቲት ሙሉካ፤ጊስቲት ሸምሲያ፤ ጊስቲት ጧህረት፤ ጊስቲት ኢቴ ዛባሬ፤ጊስቲት መኩለ ሲሆን እንዲሁም የአምስቱ ምሶሶዎች ስያሜም ኢማም ሲዴ፤ገራድ አበኬ፤መልገ ጌሎ፤ሀጅ አሊዬ ፤ሸህ ነስረላ እና አንዱ ትልቁ ምሶሶ ስያሜም የስልጤ አባት ተብለው በሚታወቁት ሀጅ አሊዬ ስም የተሰየመ ነው፡፡ሙዚየሙ የስልጤ የባህል ቤት ምርጥ አሰራር በሚባለው በሙጌ የተሰራ ነው፡፡ቁረት ማለት የቤቱን የላኛውን ሳሩን የሚሸከም ነው፡፡የስልጤ የባህል ቤት የሙዚየሙ የላይኛው ክፍል ጣሪያው (ቁረት) ቫርኒሽ ተቀብቶ ጠቆር ያለ ቀለም የያዘ ነው፡፡ያም ደሞ የስልጤ የባህል ቤት የቆየ ጥቀርሻ የለበሰ ቤትን ለማሳየት ተብሎ ነው፡፡ ምሶሶውን ይዞ ቁረቱን ደግፎ የያዘው ወጋ ይባላል፡፡ሙዚየሙ 4 የተለያዩ አስተዳደር ክፍል፤ ላይብረሪ ፤እቃ ማስቀመጫና የእንግዳ ማረፊያ የያዘ ነው፡፡

Map Location
ተመሳሳይ መስህቦች
ታግ
በማህበራዊ ሚዲያ ይቀላቀሉን
Subscribe ያድርጉ

በየ እለት የሚለቀቁ ዜናዎች ይደርስዎታል