የወራቤ ስፔሻላይዝድ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል

የወራቤ ስፔሻላይዝድ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል ለአይን በሚስብ መልኩ በ14 ሄ/ር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን የእንግዳ መቀቢያዎች (guest house) 11 ትልልቅ (ባለፎቅ) ህንፃዎች/ብሎኮች/፣ መደበኛ የሆኑ ብቻ 584 አልጋዎች እንዲሁም በ2ኛ የግንባታ ምዕራፍ የነርሶች ማሰልጠኛ ኮሌጅይ ኖረዋል፡፡ የወራቤ እስፔሻላይዝድ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል በርካታ ክፍሎችን የያዘ ሲሆን 3 ዓይነት ፋርማሲዎችንም በውስጡ ይዟል፡፡ የመጀመሪያው ፋርማሲ እንደማንኛውም ሆስፒታል መደበኛ ፋርማሲ ሲሆን 2ኛው ደግሞ ትልቅና እንደከነማ ፋርማሲዎች ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡ 3ኛው ፋርማሲ ደግሞ በስልጤ ልማት ማህበር የሚደጎምና ከውጪ የሚገቡና በአካባቢው በቀላሉ የማይገኙ መድሀኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብ ነው፡፡ሆስፒታሉ የተጎዱ ታካሚዎችና መደበኛ /ተመላላሽ/ ታካሚዎች የሚገቡባቸው የተለያዩ መግቢያ በሮች አሉት፡፡ ከዚህም ሌላ የኤሌክትሮኒክስና የኬሚስትሪ የሚባሉ 2 ላብራቶሪዎች ያሉት ሲሆን ቀዶ ጥገና ክፍሉ በአንድ ጊዜ 4 ሰው ማስተናገድ ይችላል፡፡ ኢንቴንሲቭ ኬር ዩኒት/ICU/ የሚባለው 72 ክፍሎች ያሉት ሲሆን በድምሩ 694 ዘመናዊ የታካሚ መኝታ ክፍሎችን ይዟል፡፡ ክፍሎቹ ግድግዳ ላይ ኦክስጂን የሚያቀርቡ መሳሪያዎች የተገጠሙለት ሲሆን አካል ጉዳተኞችን በቀላሉ የሚያስተናግድ መሆኑም ልዩ ያደርገዋል፡፡ ይህ ሆስፒታል በህዝብ ተሳትፎ በስልጤ ልማት ማህበር አስተባባሪነት የተገነባ እጅግ ዘመናዊና የህዝብ አሻራ ያረፈበት ብቻም ሳይሆን በሀገራችን health tourism(የጤና ቱሪዝምን) ለማስፋፋት አስተዋጽኦ የጎላ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሆስፒታል ነው፡፡ ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶች በርካታ መሆናቸው የጤና ቱሪዝም ዘርፉን ተቋሙ የሚያካትት መሆኑን አመላካች ነው፡፡

Map Location
ተመሳሳይ መስህቦች
ታግ
በማህበራዊ ሚዲያ ይቀላቀሉን
Subscribe ያድርጉ

በየ እለት የሚለቀቁ ዜናዎች ይደርስዎታል