Post Thumbnail
የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በመስራት የተበላሹና ጠፍ መሬቶችን ወደ ለምነት መቀየር ይገባል ፦ አቶ ዘይኔ ብልካ!

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ዘይኔ ብልካ ይህን ያሉት በስልጤ ዞን የ2017 የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ዞናዊ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በላንፉሮ ወረዳ በወታንቦ ጎቤ ቀበሌ ቆሜ ልማት ቡድን በይፋ በስጀመሩበት ወቅት ነው።

በተፋሰስ ልማት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ብልካ የተፋሰስ ልማት ስራ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያሳድረውን አሎታዊ ተፅዕኖ በመቀነስ ለምርትና ምርታማነት እድገት ዓይነተኛ አበርክቶ እንዳለው ገልፀዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም የዞኑ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራው በተጠናከረ መልኩ መሰራትና በዚህም ችግኝ በመትከል የማር ንብ እና ልዩ ልዩ የፍራፍሬ አትክልቶች እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የተፋሰስ ስራ ሲሰራ ትምህርትን ለማጠናከር ፣የመንገድ ስራ ለማጠናከር፣ ጤናን ለማጠናከር፣ የመስኖ ስራን ለማሻሻል እና ለማጠናከር እንዲሁም በየአካባቢው ወጣ ያለ ነገር ሲታይ አብሮ በውይይት ለመፍታት ሁነኛ ስራ እንደሆነ አንስተዋል።

ወረዳው በተፋሰስ ልማት ስራው ብቻ ሳይሆን የፀደይ ልማት ላይ በሽንብራ እና በሌሎች ፍራፍሬዎችንና የጓሮ አትክልቶች የተሻለ አፈፃፀም እያስመዘገ የሚገኝ ወረዳ እንደሆነ አንስተዋል።

የዞኑ ምክትል አስተዳደሪና የግብርና መምሪያው ዋና ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል በዙኑ የተፋሰስ ልማት ከዘመቻ ስራነት ወደ በህልነት እየተቀየረ መምጣቱን አንስተዋል።

በዘንድሮ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራችን በ237 ነባር ንዑስ ተፋሰሶች ውስጥ በሚገኝ 35,158 ሄ/ር መሬት ላይ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

ባለፉት አመታት በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል ያሉት ምክትል አስተዳደሪው የስነ አካላዊና የስነ ህይወታዊ ስራዎች በመሰራታቸው የአፈር መሸርሸር እንዲቀንስ ተደርጓል እንዲሁም የተራቆቱ አካባቢዎች በማገገም ወደ አረንጓዴነት ተቀይሯል።

በተቀናጀ ተፋሰስ ልማት የለሙ ተራሮች ወደ ገንዘብ ማተሚያነት እየተቀየረ እንደሆነና ለወጣቱ ስራ እድል መፍጠሪያ ፣ለመኖ ልማት፣ ለፍራፍሬ ልማት ለንብ ሀብት ልማትና ለሌማት ትሩፋት አገልግሎት ላይ ውሏል ብለዋል።

ከተፋሰስ ልማት ስራው ጎን ለጎን የኮሪደር ልማት፣ የሌማት ትሩፋት ስራውን እና ሌሎችን አጠናክሮ ማስኬድ ያስፈልጋል ብለዋል። የላንፉሮ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ ሸምሴ ጉንዳ የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ስለ ወረዳው የአየር ፀባይ ሁኔታ ለታዳሚዎች ገለፃ አድርገዋል።

በሌላ በኩል በወረዳ እየለሙ ያሉ የፀደይ ልማት ስራዎችን እና ልዩ ልዩ ልማታዊ ተግባራትን ጉብኝት አድርገዋል።

በተፋሰስ ልማት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ብልካ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ፣የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል ፣የዞኑ የፖለቲካና ሪዕዮተ አለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሸረፋ ሌገሶ እና የዞኑ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳሊያ ሀሳን እና የወረዳው ዋና አስተዳደሪ አቶ ሸምሴ ጉንዳን ጨምሮ ሌሎች የዞንና የወረዳ የስራ ኃላፊዎች የወታንቦ ጎቤ ቀበሌ አርሶ አደሮችን ታድመዋል።

0 አስተያየቶች

አስተያየትዎን ይጻፉልን