Post Thumbnail
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2ኛ ዙር ሰልጣኝ አመራሮች በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ሶጃት የኢንዱስትሪ መንደርን ጎበኙ!

በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካና በዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር የተመራው ልዑክ በዛሬው ዕለት በወራቤ ከተማ ሶጃት የኢንዱስትሪ መንደርን በአካል ተገኝተው ጎብኝተዋል።

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ዘይኔ ብልካ በጉብኝቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ለሀገሪቷ ለተለያዩ አካባቢዎች ምርት የምናቀርብበት የኢንዱስትሪ መንደር እንደሆነ ለጎብኚዎች ገልጸዋል።

ገንዘብ እውቀት እና ኢንተርፕረነርን በአንድ ላይ እየሰራን እንገኛለን ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በዚህም የቅባት እህል ፣ ቅመማ ቅመም፣ በትንሽ ቦታ ብዙ ምርቶችን የምናመርትበትን ሁኔታ እየፈጠርን ነው ብለዋል።

ኢንዱስትሪ መንደሩ ከሀገሪቱ መዲናና ከዋና ዋና መንገዶች በቅርብ ርቀት መገኘቱ በቀጣይ ጊዜያት የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተሳለጠ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርም አቶ ዘይኔ አንስተዋል።

በንድፈ ሀሳብና በነባራዊ እውነታዎች ተደግፎ በሚሰጠው ስልጠና በየደረጃው ያለው አመራር ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ሁኔታዎችን ተገንዝቦ ወቅቱን የዋጀና ውጤታማ አመራር ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል።

በጉብኝት መርሃ ግብሩ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ዘይኔ ብልካ፣ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የሰልጣኝ ቡድኑ መሪ ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር፣ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማልና ሌሎች ሰልጣኝ አመራሮች ተሳትፈዋል።

0 Comments

Leave A Comment