Post Thumbnail
የስልጤ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የባለፉት 4 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄደ

የስልጤ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የባለፉት 4 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄደ!

የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት በስልጤ ባህል አዳራሽ የ2017 በጀት ዓመት የባለፉት 4 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሂዷል። የውይይት መድረኩን የመሩት የስልጤ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ረሻድ ሙክታር እና የመልካም አስተዳደርና አካባቢ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡመር ሱሩር ናቸው።

በመድረኩ ላይ የባለፉት አራት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የሩብ ዓመት ግብረ መልስ በዝርዝር ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። ህብረተሰቡ የሚያነሷቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ እያገኙ መምጣታቸው በውይይት መድረኩ ላይ ተመላክቷል።

ጽ/ቤቱ በስራ አፈፃፀሙ ሂደት ያጋጠሙ አንኳር ችግሮችና ተግዳሮቶች አፅንኦት ሰጥቶ በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀምጧል። በውይይት መድረኩ ላይ ከሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤቶች የተውጣጡ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣የህዝብ ክንፍና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

0 Comments

Leave A Comment