
በፎረሙ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ብልካን ጨምሮ ሌሎች የዞን፣የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ባለሀብቶች ተሳትፈውበታል።
በዚህ ዞናዊ ልዩ የኢንቨስትመንት ፎረም በዞኑ አጠቃላይ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች፥ የዞኑ እምቅ የኢንቨስትመንት አቅሞች እና በዘርፉ ማነቆዎችና የትኩረት መስኮች ላይ ከባለሀብቱና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር የሚመከርበት እንደሆነ ተነግሯል።
በዝግጅቱ ላይ እስካሁን ያሉ የኢንቨስትመንት ስራዎችና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ምክክር እየተደረገበት ይገኛል።
Leave A Comment